እስራኤል በሐማስ ላይ የምታካሂደው ጦርነት ተጠናክሮ በቀጠለበት ወቅት፣ የማላዊ መንግስት ወጣቶችን በእስራኤል እርሻ ስራ ላይ እንዲሰማሩ ወደ እስራኤል እየላከ ነው። ተቺዎች መርሐ ግብሩ በሚስጥር መካሄዱን በመግለፅ የተቃወሙ ሲሆን፣ ማላዊ ውስጥ ያለውን የስራ አጥነት ችግርም ያጋለጠ ነው ብለዋል።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በበኩላቸው፣ ወጣቶች ምንም ዐይነት አደጋ ቢኖር ወደ ውጪ ሀገር የመሄድ እድል ሲያገኙ ለመጠቀም ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ከማላዊ ዋና ከተማ ከሊሎንግዌ በቺምሜዌ ፓዳታ የተጠናቀረውን ዘገባ ስመኝሽ የቆየ ወደ ዐማርኛ መልሳዋለች፡፡
መድረክ / ፎረም