ዋሺንግተን ዲሲ —
ሁለት ትልልቅ የማላዊ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመጪው ግንቦት ወር በሚካሄደው ምርጫ አብርው ለመወዳደር ኅብረት መፍጠራቸው ተዘግቧል። ሁለቱ ፓርቲዎች ባቀረቡት ክስ ምክንያት ባለፈው ዓመት የተካሄደው ምርጫ ውጤት ተሰርዞ እንደገና ምርጫ እንዲካሄድ አንድ ፍ/ቤት አዟል።
የማላዊ ኮንግረስ ፓርቲና የተባበረው የትራንስፎርሜሽን ንቅናቄ ሥምምነቱን በቅርቡ ፈርመው ለፕሬዚዳንትነትና ለሌሎች ቦታዎች የሚወዳደሩ ሰዎችን እናቀርባለን ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ