በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማላዊ የኢትዮጵያውያን ነው በተባለው የጅምላ መቃብር ጉዳይ ምርምራው ቀጥሏል


ፎቶ ፋይል፦ በማላዊ የተገኘው ጅምላ መቃብር
ፎቶ ፋይል፦ በማላዊ የተገኘው ጅምላ መቃብር

በማላዊ ከጅምላ መቃብር ጋር በተያያዘ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ፒተር ሙታሪካ የእንጀራ ልጅ የሆኑት ታዲኪራ ማፉብዛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።

በአንድ ጫካ ውስጥ የተገኘው የጅምላ መቃብር፣ ወደ ደቡብ አፍሪካ ያመሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ አይቀሩም ሲል ፖሊስ በወቅቱ አስታውቆ ነበር።

ፖሊስ እንደሚለው ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት ከጅምላ መቃብሩ ጋር በተያያዘ በሚያደርጉት ምርመራ ነው።

ታዲኪራ እራሳቸውን ለፖሊስ ትናንት ረቡዕ አስረክበዋል።

አንዳንድ የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያዊ ፍልሰተኞቹን ወደ ደቡብ አፍሪካ በማጓጓዝ የተጠረጠረ መኪና ፖሊስ መያዙን በመዘገብ ላይ ናቸው።

ፖሊስ ባደረገው የቅድሚያ ምርመራ፣ ከሟቾቹ ላይ ኢትዮጵያዊ የመጓጓዣ ሰነድ እንዲሁም የኢትዮጵያ የልስክ ሲም ካርድ ማግኘቱን በወቅቱ አስታውቆ ነበር።

XS
SM
MD
LG