በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማላዊ በኮሌራ ወረርሽኝ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞቱ


የጤና ባለሞያዋ የኮሌራ ክትባት እየሰጡ
የጤና ባለሞያዋ የኮሌራ ክትባት እየሰጡ

ከሁለት አስርት ዓመታት ወዲህ በተከሰተ አስከፊ የኮሌራ ወረርሽኝ የ750 ሰዎች ህይወት ማለፉን የማላዊ መንግሥት አስታወቀ።

የዓለም ጤና ድርጅትም በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው እና 'ከተለመደው በበለጠ በጣም የተስፋፋ እና ገዳይ' በሆነው በዚህ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ ከተጠቁ ሀገሮች መካክል ማላዊ አንዷ መሆኗን አስታውቋል።

የማላዊ ጤና ሚኒስቴር ሐሙስ እለት ባወጡት ትዕዛዝ የንጹህ ውሃ፣ የመጸዳጃ ቤት እና የቆሻሻ ማስወገጃ የሌላቸው የንግድ ተቋማት እንዲዘጉ ያሳሰቡ ሲሆን ያልበሰሉ ምግቦች ሽያጭ ላይም ገደቦች አስቀምጠዋል።

የጤና ሚኒስትሩ እንደገለፁት ውሃ ወለድ በሆነው በሽታ አዲስ ከተያዙ 589 ህሙማን ውስጥ 17ቱ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ህይወታቸው አልፏል።

ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር በሽታው በማላዊ መከሰቱ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን 22ሺህ 759 ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን በየቀኑ 15 ሰዎች ህይወታቸው ያልፋል። ባለፉት አስር ቀናት ውስጥም 155 ሰዎች መሞታቸው ተመዝግቧል።

XS
SM
MD
LG