በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወባ በገዳይነታቸው ከሚታወቁ በሽታዎች አንዱ ነው


በዋናነት በቆላማ አካባቢዎች ተስፋፍቶ የሚገኘው ወባ ባለፉት ዓመታት የአልጋ አጎበር ሥርጭት በመስፋፋቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ሥርጭቱ እየቀነሰ መምጣቱን የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ከኢትዮጵያ ህዝብ 68 ከመቶ የሚሆነው ለወባ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖር ሲሆን በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር በ2017 ዓ.ምም 2 ሚሊየን ተኩል ሰው በወባ መያዙ ተዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ወባን ለመቆጣጠር ብቻ ሳይሆን ከመላ ሃገሪቱ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት አቅዶ እየሠራ እንደሚገኝ ተናግሯል።

ይሄንን ዕቅድ ለማሳካት ደግሞ በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች ያሉ ወባ አምጪ ተውሣክ እና የወባ ትንኝ ዓይነቶች ጥናት በየደረጃው ይካሄዳል።

በመስኩ እየተደረጉ ናቸው የሚባሉት ጥረቶችን ሊያግዝ እንደሚችል የተነገረ ግኝት ላይ እሠየራ ያለ ወጣት ተመራማሪን የድሬዳዋው ሪፖርተራችን አዲስ ቸኮል ሰሞኑን አነጋግሯል። ተመራማሪው ኢትዮጵያ ውስጥ ቀድሞ የማትታወቅ የቢምቢ ዝርያ አግኝቷል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

ወባ በገዳይነታቸው ከሚታወቁ በሽታዎች አንዱ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:00 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG