በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማርጀሪ ስቶንማን ዳግላስ ት/ቤት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመለሱ

በዩናትድ ስቴትስ ታሪክ ከምንጊዜውም ቁጥሩ የበዛ ህይወት በጥይት የጠፋበት የፍሎሪዳው ትምህርት ቤት ከጥቃቱ የተረፉት ተማሪዎች ዛሬ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል።

በዩናትድ ስቴትስ ታሪክ ከምንጊዜውም ቁጥሩ የበዛ ህይወት በጥይት የጠፋበት የፍሎሪዳው ትምህርት ቤት ከጥቃቱ የተረፉት ተማሪዎች ዛሬ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል።

የፌዴራሉ መንግሥትና እና የክፍላተ ሀገር ባለሥልጣናት በበኩላቸው ወጣቶችን ደኅንነታቸው ሊጥበቅላቸው በሚገባባቸው ትምህርት ቤቶች ህይወታቸውን እንዳያጡ ለመከላከል ምን ማድረግ ይገባናል በሚለው ጉዳይ ክርክራቸውን ቀጥለዋል።

ከሁለት ሳምንታት በፊት በታጠቀ አጥቂ ጥይት አሥራ ሰባት ሰው የተገደለበት የፍሎሪዳው ማርጀሪ ስቶንማን ዳግላስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እስካሁን ተዘግቶ ቆይቷል።

በዚያ ትምህርት ቤት የደረሰው ፍጅት በሀገሪቱ ረጅም ታሪክ ያለውን የመሳሪያ ባለቤትነትና ተያያዝ ጉዳይ ክርክር አቀጣጥሎታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG