በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶር. ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ፣ ዛሬ ኀሙስ፣ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ማለዳ፣ ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መታሰራቸውን ማኅበሩ እና ቤተሰቦቻቸው ገለፁ።
የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል ጽሕፈት ቤት፣ በፌስቡክ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ፤ ሁለቱ ኃላፊዎች፣ ሜክሲኮ የሚገኘው ፌዴራል ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚገኙ እና መኖሪያ ቤታቸውም መፈተሹን አስፍሯል።
የሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶር. ሙሉጌታ ሥዩም ባለቤት ወሮ. ዓይናለም እና የዋና ጸሐፊው መምህር ዋሲሁን በላይ ባለቤት ወሮ. ዘውድነሽ አዱኛ፣ የማኅበሩ ኃላፊዎች፣ በዛሬው ዕለት መወሰዳቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
ጠዋት ተይዘው በተወሰዱበት ወቅት፣ እርሳቸው ሥራ ቦታ እንደነበሩ የተናገሩት የማኅበሩ ሰብሳቢ፣ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም ወ/ሮ ዓይናለም፣ ባለቤታቸውን እስከ አሁን እርሳቸውም ይኹን ቤተሰቦቻቸው እንዳላገኟቸው ገልጸዋል፡፡የባለቤታቸውን መታሰርም ከልጆቻቸው መስማታቸውን ተናግረዋል።
የመምሕር ዋሲሁን በላይ ባለቤት፣ ወ/ሮ ዘውድነሽም ቢኾኑ የባለቤታቸውን መታሰር ከማረጋገጥ ውጪ ተጨማሪ መረጃም አልሰጡንም። አድማጮች በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ ይዘን እንመለሳለን።
መድረክ / ፎረም