የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን እአአ በ1996 በከፍተኛው የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማትነት እንዲያገለግሉ የመረጧቸው ማድሊን ኦልብራይት፣ ክሊንተን ሥልጣን ላይ ከቆዩባቸው ስምንት ዓመታት በመጨረሻዎቹ አራቱ 1996 እስከ 2000 የአውሮፓ ዓመት ነው በኃላፊነቱ ያገለገሉት።
ኦልብራይት በወቅቱ፣ በዚያ ኃላፊነታቸው በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ታሪክ ከከፍተኛው የሥልጣን ደረጃ የደረሱ ሴት ነበሩ። ይሁንና የቀድሞዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የውጭ አገር ተወላጅ በመሆናቸው በፖለቲካው ገፍተው በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የመሳተፍ ዕድል አልነበራቸውም። ኦልብራይት የተወለዱት ከቀድሞዋ ቼኮዝሎቫኪያ ውስጥ ነበር።
ማድሊን ኦልብራይት ባደረባቸው የካንሰር ህመም ሲደረዱ ከቆዩ በኋላ በተወለዱ በ84 አመታቸው በዛሬው ዕለት ማረፋቸውን ይፋ ያደረጉት ቤተሰቦቻቸው፤ በትዊተር ባሰፈሩት መልዕክት፣ ኦልብራይት ባረፉበት ወቅት "በቤተሰብ እና ጓደኞቻቸው እንደተከበቡ ነበር" ሲሉ ነበር ብለዋል።