በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በማዳጋስካር ቶማሲና


የማዳጋስካር ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ ቶማሲና ውስጥ የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር እያሻቀበ በመምጣቱ የሀገሪቱ መንግሥት ወታደሮችና ሐኪሞች እየላከ መሆኑ ተገለጸ። ማዳጋስካር ባለፈው ሳምንት ሃሙስ ውስጥ የቫይረሱ ተጠቂዎች በ122 መጨመሩን አስታውቃለች።

ማዳጋስካር ከአንድ መቶ የሚበልጡ ወታደሮችን ወደ ከተማዋ ያዘመተችው ፀጥታ እንዲያስከብሩ፣ ነዋሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ የመጠቀም እና አካላዊ ርቀት የመጠበቅ ግዴታቸውን ማክበራቸውን ለማረጋገጥ መሆኑን አስታወቃለች። የሀገሪቱ በኮቪድ-19 ግብረ ኃይል ቃል አቀባይ ሲናገሩ በቅርቡ በደሴቲቱ የሞቱ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ይሁን በሌላ በሽታ ዶክተሮች የማጥራት ሥራ ይሰራሉ ብለዋል።

ቶሚሲና ከተማ ጎዳናዎች ላይ አስከሬኖች አይተናል፣ በምን ምክንያት የሞቱ መሆናቸውን አናውቅም ሲሉ አንዳንድ የዐይን እማኞች መናገራቸውን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG