በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ የኦሎምፒክ ጨዋታዎችን ኢላማ ለማድረግ ትሞክራለች - ማክሮን


ፎቶ ፋይል፦የፈረንሣይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን
ፎቶ ፋይል፦የፈረንሣይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን

የፈረንሣዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ ሩሲያ ከወራት በኋላ በፓሪስ የሚደረገውን የኦሎምፒክ ዝግጅት ኢላማ ልታደርግ እንደምትሞክር ጥርጥር እንደሌላቸው ዛሬ ሐሙስ ተናግረዋል።

የማክሮን ንግግር፣ የኦሎምፒክ ጨዋታዎችን ኢላማ ያደረገና ከውጪ የሚመጣን አደጋ በተመለከተ በግልፅ ያስታወቁበት እንደሆነ ተነግሯል።

ሩሲያ የኦሎምፒክ ጨዋታዎቹን ኢላማ ታደርግ እንደሆነ ከጋዜጠኛ ጥያቄ የቀረበላቸው ማክሮን፣ “ምንም ጥርጥር የለኝም” ሲሉ ተደምጠዋል።

የሩሲያ እና የቤላሩስ ስፖርተኞች ካለ ሃገራቸው ባንዲራና ብሔራዊ መዝሙር በግል እንደሚወዳደሩ ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ መወሰኑን ተከትሎ፣ ሩሲያ ከኮሚቴው ጋራ ያላት ግንኙነት ሻክሯል።

ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ፣ የሃገሪቱ ስፖርተኞች በዓለም አቀፍ ውድድር እንዳይሳተፉ ተከልክለው ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የፈረንሣይ ፖሊስ፣ ከፓሪስ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ፊት ለፊት ከሚገኘው ሥፍራ ላይ የነበሩና በደርዘን የሚቆጠሩ ፍልሰተኞችን አንስቷል።

በአብዛኛው ሕፃናት እና ሴቶች የሆኑና 50 የሚሆኑት ፍልሰተኞች በአውቶብስ ተጭነው ወደ ምሥራቅ ፈረንሣይ ተወስደዋል። ፍልሰተኞቹ ከፈረንሣይኛ ተናጋሪ የምዕራብ አፍሪካ ሃገራት የመጡ እንደሆነ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG