በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩክሬን ጦርነቱ ቢቀጣጠልም ማክሮን ፑቲን ላይ እስካሁን በር አልዘጉም


የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን

ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች ወዲህ አብዛኛው ዓለም ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን እየራቃቸው ቢሆንም፤ ከዓለም መሪዎች አንዱ ግን በተለይ ይህን አላደረጉም። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ሊነጋገሩ የሚችሉበት የግንኙነት መስመር ክፍት አድርገዋል።

ጦርነቱን ለመከላከል ያደረጉት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አልተሳካም። ይሁን እንጂ ማክሮን ተስፋ አልቆረጡም። በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ባለፈው የካቲት 24 የሩሲያ ኃይሎች ዩክሬን ካጠቁ ወዲህ ብቻ ሁለቱ ሰዎች አራት ጊዜ በስልክ ተነጋግረዋል።

የቅርብ ጊዜው የስልክ ጥሪያቸው ትናንት እሁድ ያደረጉት ነው። ንግግራቸውም በዩክሬን የኑዩክሌር ጣቢያዎች ደህንነት ላይ ያተኮረ ነበር። ሆኖም በዩክሬን ለሚደርሰው የሰዎች ሞት እና ውድመት፤ ብሎም ጦርነቱ በአውሮፓ ላይ በሚያስከተለው መጠነ ሰፊ መዘዝ ተጠያቂው ፑቲን ብቻ መሆናቸውን ማክሮን ገና ከጅምሩ ግልጽ አድርገዋል።

XS
SM
MD
LG