በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የምጣኔ ኃብት ማሻሻያ ለማድረግ ቃል ገቡ

ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን
ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን

ፈረንሣይን ሲንጣት ከከረመው ፀረ-መንግሥት ተቃውሞ በኋላ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ወጥተው ባደረጉት ንግግር በርካታ የምጣኔ ኃብት ማሻሻያ ቃሎች ገብተዋል። ይሁን እንጂ ሥልጣናቸውን እንደማይለቅቁ ተናግረዋል።

ፈረንሣይን ሲንጣት ከከረመው ፀረ-መንግሥት ተቃውሞ በኋላ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ወጥተው ባደረጉት ንግግር በርካታ የምጣኔ ኃብት ማሻሻያ ቃሎች ገብተዋል። ይሁን እንጂ ሥልጣናቸውን እንደማይለቅቁ ተናግረዋል።

“በርግጥ ሰዎችን በንግግሮቼ አስቀይሜ ሊሆን ይችላል፤ ለዚህ የራሴን ኃላፊነት እወስዳለሁ” ብለዋል ማክሮን በዛሬው ንግግራቸው።

የግብር ጭማሪ ሃሣባቸውም “ፍትሃዊ አይደለም” ሲሉ አምነዋል። ይሁን እንጂ የሰሞኑ ቁጣ የገነፈለው ላለፉት አርባ ዓመታት በተለይ በገጠሪቱ ፈረንሣይ ሲንተከተክ ከቆየ በኋላ ነው ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG