በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈረንሳዩ ማክሮን ቻይና ይገኛሉ


የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በቻይና ቤጂንግ የሚገኘ ሙዚየም ሲጎበኙ
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በቻይና ቤጂንግ የሚገኘ ሙዚየም ሲጎበኙ

ቻይና በዩክሬንና በሌሎችም ግጭት ባሉባቸው የዓለም ክፍሎች ሰላምን በተመለከተ በጋራ ሃላፊነት እንድትወስድ የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግን በሚያገኙበት ወቅት አጽንኦት እንደሚሰጡት የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ዛሬ ተናግረዋል፡፡

በቻይና የፈርንሳይ ኤምባሲ በመገኘት ለአገራቸው ዜጎች ንግግር ያደረጉት ማክሮን፣ ዩክሬን፣ ኢራን እና ሰሜን ኮሪያን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን፣ በተለይም ሰላምን በሚመለከት ቻይና በጋራ ሃላፊነት የምትወስድበትን ሁኔታ ከፕሬዚዳንት ሺ ጋር በሚኖራቸው ውይይት ትኩረት እንደሚሰጡት አስታውቀዋል፡፡

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሰላ ቮንደር ላይን ከማክሮን ጋር አብረው ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ የአውሮፓን አንድነት ለማሳየት ነው ተብሏል፡፡

በጉብኝታቸው ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሂደው ጦርነት ዋና አጀንዳ እንደሚሆን ይጠበቃል ሲል አሶስዬትድ ፕረስ በዘገባው አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG