በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማክሮን አልጄሪያ ጉብኝት

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት አማኑኤል ማክሮን ለሦስት ቀናት ጉብኝት አልጄሪያ ገብተዋል። የጉብኝቱ ዓላማ የወደፊት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን ለማሳደግና፣ በ132 ዓመታት ቅኝ ግዛት ወቅት የተፈጠረውን ቁስል ለማዳን ነው ሲል አሶስዬትድ ፕረስ ዘግቧል።

ጉብኝቱ የመጣው አንድ ወር ተኩል የቆየው ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ከተፈጠረ ዓመት ሳይሞላው መሆኑን ነው።

አሶሲዬትድ ፐርስ በዘገባው እንዳለው የዩክሬኑ ጦርነት አልጄሪያን ወሳኝ ቦታን እንድትይዝ በር ከፍቷል። ሃገሪቱ ለአውሮፓ አህጉር ነዳጅ ላኪ በመሆን ቁልፍ ቦታ ይዛለች።

እአአ ከ1954 እስከ 1962 ባሉት ዓመታት ውስጥ በአልጄሪያ በነበረው የነጻነት ጦርነት ወቅት የፈረንሳይ ወታደሮች ሰቆቃና ግድያ መፈጸማቸውን ባለፉት ዓመታት ማክሮን እውቅና በመስጠት ከዚህ በፊት ያልታየ እርምጃ ወስደዋል ሲል ኤፒ ዘግቧል። ቢሆንም ፈረንሳይ በጦርነቱ ወቅት ለፈጸመችው ሰቆቃና ግድያ ይቅርታ ትጠይቅ ለሚለው የአልጄሪያ ጥያቄ በቂ መልስ አይደለም ተብሏል።

ማክሮንና የአልጄሪያው ፕሬዚዳንት አብደልማጂድ ታቡን በጦርነቱ ወቅት ህይወታቸውን ያጡ ወታደሮች መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

ማክሮን ከጦር አዛዣቸው ጋር በመሆን ከፕሬዚዳንት አብድልማጂድ ጋር የቀጠናውን ሰላምና መረጋጋት በተመለከተ ለሁለተኛ ስብሰባ እንዲምቀመጡ ይጠበቃል። ፈረንሳይ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከማሊ ጦሯን አውጥታ አጠናቃለች።

ህገ-ወጥ አስተላላፊዎችና እስላማዊ አክራሪዎች ባሉበት ቀጠና፤ ከማሊ፣ ኒጀር እና ሊቢያ ጋር ድንበር ከምትዋሰነው አልጄሪያ ጋር መቀናጀት አስፈላጊ ነው ተብሏል።


ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG