በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሉዊዚያና አሥርቱ ትዕዛዛት በትምህርት ክፍል ውስጥ እንዲሰቀል የሚያዝ አዋጅ ጸደቀ


ሪፐብሊካዊው ሃገረ ገዥ ጄፍ ላንድሪ
ሪፐብሊካዊው ሃገረ ገዥ ጄፍ ላንድሪ

በአሜሪካ በሉዊዚያና ግዛት አሥርቱ ትዕዛዛት በሕዝብ ትምህርት ቤት ክፍሎች ውስጥ እንዲሰቀል ትላንት ረቡዕ በአዋጅ ተደንግጓል።

ውሳኔው በሪፐብሊካኖች ቁጥጥር ሥር ያለው የግዛቲቱ የሕግ አውጪ ም/ቤት የወግ አጥባቂዎችን አጀንዳ ለማስፈጸም የወሰደው ሌላ እርምጃ እንደሆነ በመነገር ላይ ነው።

በሪፐብሊካዊው ሃገረ ገዥ ጄፍ ላንድሪ ትላንት የተፈረመው ሕግ፣ የፖስተር መጠን ያለውና በቀላሉ መነበብ የሚችል አሥርቱን ትዕዛዝ የያዘ ሰሌዳ በመንግስት በጀት በሚንቀሳቀሱና ከሕፃናት መዋያ እስከ ዩኒቨርስቲዎች ባሉ የትምህርት ክፍሎች ግድግዳ ላይ እንዲሰቀል ያዛል።

ሕጉ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ታውቋል።

የሕጉ ተቃዋሚዎች ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ በማንሳት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱ ሲያስታውቁ፣ ደጋፊዎቹ ደግሞ ሕጉ ኃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን፣ ታሪካዊ ትርጉም ጭምር እንዳለውም በመናገር ላይ ናቸው።

ከዚህ ቀደም በእ.አ.አ 1980 በኬንተኪ ግዛት የወጣውን ተመሳሳይ ሕግ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍ/ቤት ‘ሕገ መንግስቱን የሚጻረር ነው’ በሚል ውድቅ አድርጎታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG