የፓሪስ ኦሊምፒክስ ትላንት ሲተናቀቅ፣ የአሜሪካዋ ሎስ ኤንጀለስ ከተማ ቀጣዩ አስተናጋጅ በመሆኗ ችቦውን ተረክባለች፡፡
የከተማዋ ከንቲባ ኬረን ባስ ትላንት በፓሪስ ኦሊምፒክስ የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ላይ ችቦውን ተረክበዋል። ከንቲባዋ ችቦውን የሎስ ኤንጀለስ የንግድ ወኪል ለሆነው የፊልም ተዋናዩ ቶም ክሩዝ አስረክበዋል።
ሎስ ኤንጀለስ ኦሊምፒክስን ሶስት ጊዜ በማስተናገድ ሶስተኛ ከተማም ትሆናለች፡፡
በከተማዋ በቅርብ ጊዜ በብዛት የሚታየው የሕንጻ ግንባታ እገዛ እንደሚኖረው አዘጋጆቹ በመናገር ላይ ናቸው። በአንጻራዊ አዲስ የሆነው ሶፊ ስቴዲየም የመክፈቻ ሥነ ስርዓቱን እንደሚያስተናግድ ሲታወቅ፣ መቶ ዓመት የተጠጋውና ለከተማዋ የመጀመሪያውን ኦሊምፒክስ በእ.አ.አ 1932 ያስተናገድው ስፍራ፣ “ኮሎሲየም” ውድድሮችን እንደሚያስተናግድ ይጠበቃል።
ከተማዋ በእ.አ.አ 1984 ለሁለተኛ ጊዜ ኦሊምፒክስን ባዘጋጀችበት ወቅት ከነበረው የመጓጓዣ አገልግሎት የትሻለ ቢኖራትም እስከ 2028 ድረስ ተጨማሪ ግንባታ እንደምታደርግ ተነግሯል።
መድረክ / ፎረም