በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሪታንያ ፖሊሶች ለንደን ባቡር ላይ በተፈፀመው የቦምብ ጥቃት ሁለት ተጠርጣሪዎችን አሰሩ


የብሪታንያ ፖሊሶች ባለፈው ሳምንት ለንደን በሚገኘው ባቡር ላይ ከተፈፀመው የቦምብ ጥቃት ጋር በተያያዘ ሁለት ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን አሰሩ።

የብሪታንያ ፖሊሶች ባለፈው ሳምንት ለንደን በሚገኘው ባቡር ላይ ከተፈፀመው የቦምብ ጥቃት ጋር በተያያዘ ሁለት ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን አሰሩ። በጥቃቱ ከሠላሳ በላይ የሚሆኑ ሰዎች እንደቆሰሉ ታውቋል።

ባለሥልጣኖች በገለፁት መሰረት ዕድሜያቸው 48 እና 30 የሆኑት ተጠርታሪዎቹ የታሰሩት በኒው ፖርት ዌልስ ላይ ነው። ትላንት ሌሊት ደግሞ አንድ ሰው እዛው ታስሯል። በሁለቱም ቦታዎች ዛሬ ፍተሻው ቀጥሏል።

የታሰሩት ሰዎች እንዴት ከፍንዳታው ጋር እንደተያያዙ የሜትሮፖሊታኑ ፖሲስ አልገለጸም። ጥቃቱ ባለፈው አርብ ከተፈጸመ ወዲህ አምስት ሰዎች ታስረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG