በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለንደን ውስጥ ባቡር ላይ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ አሥራ ሥምንት ሰዎች ተጎዱ

ለንደን ውስጥ ዛሬ ዓርብ ማለዳ ወደስራ የሚሄዱ ተጓዦች በታጨቁበት ባቡር ላይ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ አሥራ ሥምንት ሰዎች መጎዳታቸው ተገለፀ። ብዙዎቹ በተነሳው እሳት ተቃጥለው ነው። ፖሊሶች ድርጊቱን በሽብርተኛ ተግባርነት ፈርጀው እየመረመሩ ናቸው።

ለንደን ውስጥ ዛሬ ዓርብ ማለዳ ወደስራ የሚሄዱ ተጓዦች በታጨቁበት ባቡር ላይ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ አሥራ ሥምንት ሰዎች መጎዳታቸው ተገለፀ። ብዙዎቹ በተነሳው እሳት ተቃጥለው ነው። ፖሊሶች ድርጊቱን በሽብርተኛ ተግባርነት ፈርጀው እየመረመሩ ናቸው።

ተሳፋሪዎች ቃጠሎና ፍንዳታ ተፈጥሯል ብለው ካስታወቁ በኋላ፣ የታጠቁ ፖሊሶች ወዲያውኑ ፓርሰንስ የምድር ውስጥ ባቡር ጣቢያ ገብተው ክትትል አድርገዋል። ቃጠሎው የተነሳው ከፈንጂው መሆኑን ገልጿል።

የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ሕዝቡ እንዲረጋጋ ተማፅነው ስለፍንንዳታው እንዲህ ነው ብሎ በግምት ከመናገር መቆጠብ እንደሚያስፈልግም መክረዋል።

የለንደን ከንቲባ ሳዲክ ኻን በበኩላቸው የለንደንን ሕዝብ ሽብርተኝነት አያንበረክከውም ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕም

“በለንደን ሌላ የደካማ ሽብርተኛ ጥቃት!! እነዚህ በሽተኞች እና ዕብዶች የእንግሊዝ ደኅንነት ስኮትላንድ ያርድ ሲከታተለቸው ነበር፣ መቅደም ይኖርበታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG