በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በለንደን የሶማሊያ ጉዳይ ጉባዔ ተካሄደ


የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን መጋበዝ በመቃወም ሰልፍ ተደረገ፡፡

በሶማሊያ የአሁን ጉዳይና የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ለመምከር በእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካመሮን አስተናጋጅነት ለንደን ላይ ለተጠራው ዓለምአቀፍ ጉባዔ ከተጋበዙ መሪዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አንዱ ናቸው፡፡

ለንደን ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን ሶማሌዎች ግን የአቶ መለስን በጉባዔው ላይ መገኘትና የእንግሊዝ መንግሥትም እርሣቸውን መጋበዙን በመቃወም ሐሙስ የካቲት 15/2004 ዓ.ም ከማለዳው ጀምሮ ጉባዔው በሚካሄድበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

አዲሱ አበበ ወደ ለንደን ደውሎ ከተቃውሞው ሰልፍ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑትን አቶ ዘላለም ተሰማንና ለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና ኮምዩኒኬሽንስ ኃላፊ የሆኑትን አቶ ተወልደ ሙሉጌታን አነጋግሯል፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG