በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያዊው ሹራ ቂጣታ የለንደን ማራቶን ባለድል ሆነ 


ዛሬ በተካሄደው የለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊው ሹራ ቂጣታ አሸነፈ።  ያሸንፋል ተብሎ የተጠበቀውን የአራት ግዜየለንደን ማራቶን አሸናፊ ኬንያዊው ኢሊዮድ ኪፕቾጌን አሸንፎ ነው ኢትዮጵያዊው ሹራ ውድድሩን በድል ያጠናቀቀው። 

ክፕቾጌን ይቀናቀነዋል ተብሎ የነበረው ኢትዮጵያዊው ቀነኒሳ በቀለ እግሩ ላይ በደረሰበት ጉዳት የተነሳ ራሱን ከውድድሩ ማግለሉ ይታወሳል።

ኪፕቾጌ ውድድሩን በስምንተኝነት አጠናቅቋዋል

ሹራ ቂጣታ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከአምስት ደቂቃ ከአርባ አንድ ሰኮንድ አጠናቅቆ የገባ ሲሆን ኬንያዊው ቪንሰንት ኪፕቾምባ ሁለተኛ ሆኖ ገብቱዋል።

ኢትዮጵያውያኑ ሲሳይ ለማ ፣ ሞስነት ገረመው ፣ሙሌ ዋሲሁን እና ታምራት ቶላ ከሶስተኛ እስከ ስድስተኛ ደረጃ ያለውን ስፍራ ተከተለው ይዘዋል።

በሴቶች ኬንያዊቷ ብሪጂት ኮስጌ 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በመግባት ባለ ድል ሆናለች። አሜሪካዊቷ ሳራ ሃል ሁለተኛ ፣ ኬንያዊቷ ሩት ቺፕንጊት ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን ተቆናጣለች።

XS
SM
MD
LG