በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በለንደን ባቡር ጣቢያ ፍንዳታ የ18 ዓመቱ ወጣት ክሥ ተመሰረተበት

ባለፈው ሳምንት ለንደን ውስጥ በሚገኘው የባቡር ጣቢያ በደረሰውና 20 ሰዎች ባቆሰለው የቦምብ ፍንዳታ፣ የእንግሊዝ ፖሊሶች ዛሬ ዐርብ በአንድ የ18 ዓመት ወጣት ላይ ክስ መሰረቱ።

ባለፈው ሳምንት ለንደን ውስጥ በሚገኘው የባቡር ጣቢያ በደረሰውና 20 ሰዎች ባቆሰለው የቦምብ ፍንዳታ፣ የእንግሊዝ ፖሊሶች ዛሬ ዐርብ በአንድ የ18 ዓመት ወጣት ላይ ክስ መሰረቱ።

ትውልዱ ከኢራቅ መሆኑ የተነገረው አህመድ ሁሴን በቁጥጥር ስር የዋለው፣ በመርከብ ወደ ፈረንሳይ የሚጓዙ ሰዎች ከሚሳፈሩበት ከታወቀው የዶቨር ወደብ ሲሆን፣ ተጠርጣሪው አህመድ፣ ፈንጂ ይዞ መገኘቱም ታውቋል።

አህመድ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላም ይኖርበት የነበረው ቤትም በፖሊሶች መፈተሹ ታውቋል።

በአህመድ ላይ ክስ እንደተመሰረተ ይፋ የሆነው፣ ቀደም ሲል በፍንዳታው የተጠረጠሩ አንድ የ21እና ሌላ የ48 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሁለት ሰዎች ባለፈው ቅዳሜ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG