በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአንበጣ መንጋ በኢትዮጵያ


የአምበጣ መንጋ
የአምበጣ መንጋ

በትግራይ ደቡባዊ ዞን የአንበጣ መንጋ በደረሱ አዝርእት ላይ ጥቃት እያደረሰ ነው። በተለይ በራያ ጨርጨር ወረዳ የአንበጣ መንጋው ለመቆጣጠር እየከበደ ነው ሲሉ ቪኦኤ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች ገልጸዋል።

ከክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች የአርሶ አደር ማሳ ለማዳን የአንበጣ መንጋ ወዳለበት የትግራይ ዶቡባዊ ዞን በተለይ ወጣቶች በብዛት በመሄድ እያገዙ ናቸው ተብሏል።

የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የአንበጣ መንጋ በታየባቸው አካባቢዎች ጉብኝት ባደረጉት ወቅት በሰጡት መግለጫ መንጋው ለመከላከል የሚሰራው ሥራ መጠናከር አለበት ብለው የፌደራሉ መንግሥት ግን የመከላከሉ ሥራ እያደናቀፈ ነው በማለት ከሰዋል።

የግብርና ሚኒስትር በበኩሉ በትግራይ ጨምሮ የአንበጣ መንጋ በታየባቸው አከባቢዎች የመከላከል ሥራ እየሰራሁ እንጂ እያደናቀፍኩ አይደለሁም ብሏል።

በሌላም በኩል ከመስከረም 21 ጀምሮ በተከሰተው የአንበጣ ወረርሺኝ 26 የገጠር ቀበሌዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የድሬደዋ አስተዳድር አስታወቀ። የጉዳቱ መጠን እስካሁን ተጣርቶ አለማለቁን የገለጹት የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራር እስካሁን 4ሺ ሄክታር እህልና 6ሺ ሄክታር የግጦሽ መሬት በመንጋው ወድሟል ብለዋል። የግብርና ሚኒስትር ድሮንና ሄሊኮፕተር እንደሰጣቸው የተናገሩት ከፍተኛ አመራሩ በአስተዳደሩ ግምገማ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥሩ ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአንበጣ መንጋ በኢትዮጵያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:51 0:00


XS
SM
MD
LG