በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሊንድበርግ ጉብኝት በኢትዮጵያ


የዩኤስአይዲ ረዳት አስተዳዳሪ ኢትዮጵያን እየጎበኙ ነው፡፡

በምሥራቅ ኢትዮጵያ አንዳንድ ማህበረሰቦች የቆየ የምግብ ዋስትና ችግር ቢኖርባቸውም ወደ ቀውስ ደረጃ አልወረደም ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ የልማት ትብብር ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ረዳት አስተዳዳሪ አስታወቁ፡፡

አዲስ የእርዳታ አሰጣጥ መመዘኛም በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን ታውቋል።

የዩኤስኤአይዲ የዴሞክራሲ፣ የግጭቶችና የሰብዓዊ ተራድዖ ረዳት አስተዳዳሪ ናንሲ ሊንድበርግ ይህንን ያስታወቁት ባለፈው ሣምንት ማብቂያ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ያደረጉትን የሥራ ጉብኝት ሲያጠቃልሉ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ነው፡፡

በድሬዳዋና በጅጅጋ አካባቢ አንዳንድ የገጠር ቀበሌዎችን እንደጎበኙ የተናገሩት ሊንድበርግ ድርቁ ያስከተለውን ጉዳት ጠቁመው በችግሩን የዛሬ ይዘት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የመለስካቻው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG