በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ አሜሪካን እንደሚያሳስቧት ባለሥልጣኗ ገለፁ


ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ - በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር
ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ - በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር

በኢትዮጵያ ላለፉት በርካታ ወራት የዘለቁ ሰላማዊ ሰልፎችና በመንግሥት የፀጥታ አካላት የተወሰዱ እርምጃዎች እንደሚያሳስቧት ዩናይትድ ስቴትስ በተደጋጋሚ ስትገልፅ ትሰማለች፡፡

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ አሜሪካን እንደሚያሳስቧት ባለሥልጣኗ ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:39 0:00

በኢትዮጵያ ላለፉት በርካታ ወራት የዘለቁ ሰላማዊ ሰልፎችና በመንግሥት የፀጥታ አካላት የተወሰዱ እርምጃዎች እንደሚያሳስቧት ዩናይትድ ስቴትስ በተደጋጋሚ ስትገልፅ ትሰማለች፡፡

በአንድ ጎን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታው በእጅጉ የከፋ እንደሆነ በመብቶች ተሟጋች ቡድኖችም ሆነ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ዓመታዊ ሪፖርቶች የሚወቀሰው የኢትዮጵያ መንግሥት በልማትና በፀረ-ሽብር ዘመቻ የዋሽንግተን አጋር ነው።

ባለፈው ሳምንት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ዩናይትድ ስቴትስና ኢትዮጵያ በስደተኞችና ፍልሰተኞች መልሶ ማቋቋምና የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴን ለመፍጠር አብረው ለመሥራት ተስማምተዋል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስና በኢትዮጵያ ግንኙነት ዙሪያ የኦባማ አስተዳድር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “በኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሚፈፀሙ ግድያዎች፣ እስራቶችና የመብቶች ረገጣዎች የዩናይትድ ስቴትስን መንግሥት ያሳስበዋል” ብለዋል፡፡

ሚስ ቶማስ-ግሪንፊልድ አክለውም “ሁኔታዎቹ በእጅጉ ያሳስቡናል፤ ከኢትዮጵያ መንግሥት ክፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በጣም የተጋጋለ ውይይት አድርገናል። መንግሥቱ በዜጎች ለሚቀርቡ ሥጋቶችና ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥም አበረታትተናል። ሕዝቡ በተለይ ወጣቶች በመንግሥቱ ላይ ያላቸውን ቅሬታዎች የሚገልፁበት መድረክ ለመፍጠር መንግሥቱ አማራጮች እንዲወስድ ጠይቀናል። ባለፉት ሁለት ወራት እንዳየነው ሰልፎች ወደ ጥፋት እንዳያመሩ ያለንን ፍላጎት ገልፀልናቸዋል።” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባ አንደኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በስደተኞችና ፍልሰተኞች ዓለምአቀፍ ትብብር አብይ አጋር ሆኖ ከፕሬዝደንት ባራክ ኦባማና ከአውሮፓ እንዲሁም ሌሎች ሀገሮች ጋር በቅርበት መሥራቱ ተዘግቧል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የሦስት ቢሊዮን ዶላር አዲስ ዓለምአቀፍ እርዳታ ሲያቀርብ የአውሮፓ ህብረትና እንግሊዝም ለኢትዮጵያ መንግሥት ቀጥተኛ የምጣኔ ሃብት ድጋፍና በአነስተኛ ወለድ ብድር ሊሰጡ ተስማምተዋል።

ኢትዮጵያ ሁለት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን እንድትገነባና ወደ ሰላሣ ሺህ ለሚጠጉ ኤርትራዊያን ስደተኞችና ፍልሰተኞች እንዲሁም ለስድሣ ሺህ ኢትዮጵያዊያን የሥራ ዕድል የምትፈጥርበት ገንዘብ ከአውሮፓ ሀገሮች አግኝታለች፡፡

ይሄንን ሁኔታ በኒውዮርክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፊት ለፊት ቆመው ሲቃወሙ ከነበሩ ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዷ “ሰሚ ቢጠፋም ድምፃችንን ማሰማታችንን እንቀጥላለን” ብላለች፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG