በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በህንድ የ8 ዓመት ዕድሜ ህፃንን ደፍረው የገደሉ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው


አንድ የህንድ ፍርድ ቤት በህንድ ካሽሚር የስምንት ዓመት ዕድሜ ህፃንን በአስከፊ ሁኔታ ደፍረው የገደሉ ሦስት ወንዶች ላይ የዕድሜ ልክ እስራት በይኗል።

ብቻዋን ፈረሶችን ትጠብቅ በነበረችበት ወቅት ጠልፈው በመውሰድ ሰቆቃ እንደፈጸሙባት በሂንዱ ቤተ-መቅደስ ውስጥ ለአምስት ቀናት እየተፈራረቁ እንደደፈርዋት በመጨረሻም በድንጋይ ፈንክተው ከገደልዋት በኋላ አስከሬንዋን ጫካ ላይ እንደወረወሩት ተዘግቧል።

ሦስቱ ተከሳሾች ጡረታ ላይ ያሉ የመንግሥት ባለሥልጣንና ፖሊስ ይገኙባቸዋል። ሦስት ሌሎች ፖሊሶች ደግሞ ማስራጃ አጥፍተዋል ተብለው የአምስት ዓመታት እስራት ተበይኖባቸዋል። አንድ ሰው በነፃ ሲለቀቅ አንድ ከዕድሜ በታች የተባለ ልጅ በሌላ ፍርድ ቤት ይቀርባል።

መርማሪዎች በገልጹት መሰረት ህፃንው ልጅ የሙስሊም አርብቶ አደር ጎሳዎች አባል ስትሆን ዒላማ የተደርገችው ማኅበረሰብዋ ሂንዱዎች የሚበዙበትን ቦታ ለቀው እንዲሄዱ ለማስፈራራት ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG