በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢሕአዴግ ሕገመንግሥቱን አይተገብርም ሲሉ ልደቱ አያሌው ተቹ


በ1987 የፀደቀው ያሁኑ የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት በገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግና በተቃዋሚዎች መካከል አንዱ የልዩነት ምክንያት ሆኖ ዘልቋል።

(ይህ ገፅ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ኮምፕዩተርዎ ከአንድ በላይ ድምፅ ማጫወቻ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ፅሁፍ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸው፡፡)

ልዩነቱ ከሕገ-መንግሥት እንደዚሁም ካተገባበሩ የሚመነጭ ነው። ይህ ደግሞ በተለያዩ መድረኮች ሲንፀባረቅ ታይቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለሣምንታት በሥራ ገበታ ላይ እንዳልነበሩ ግልፅ ሆኗል።

የመታመማቸው ሁኔታም ይፋ ሳይሆን ቆይቷል። እርሣቸው በህመምና በህክምና ላይ በቆዩባቸው ሣምንታት ሀገሪቱን ማን እየመራ መሆኑ ግልፅ እንዳልሆነ ተቃዋሚዎች ይናገራሉ።

በቅርቡ መግለጫ የሰጡት የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር በረከት ስምዖን ግን አሁንም ሀገሪቱን እየመሩ ያሉት እርሣቸው ናቸው ብለዋል።

አንዳንድ ተቃዋሚዎች ያመራር ክፍተት በተፈጠረበት በዚህ ሰዓት እንኳን ሕገ-መንግሥቱ እየተተገበረ አይደለም ሲሉ ይናገራሉ።

በእነርሡ እምነት በዚህ ሰዓት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኃይለማርያም ደሣለኝ ተተክተው መሥራት ነበረባቸው።

አሁን የተፈጠረው ሁኔታም የኢሕአዴግ መንግሥት ሕገ-መንግሥቱን እንደማይተገብር ያጋለጠ ነው ብለዋል።

ሕገ-መንግሥቱና የልዩነት ነጥቦች። በዚህ ርዕስ ላይ እንወያያለን።

ለቃለ መጠይቅ የጋበዝናቸው ኢትዮጵያዊው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው ናቸው። የቀድሞው የኢዴፓ ሊቀ መንበር አቶ ልደቱ አያሌው የዚህን ሕገ-መንግሥት አንዳንድ አንቀፆች አምርረው በመተቸት ይታወቃሉ።

“መድሎት” በተሰኘው ሁለተኛ መፅሐፋቸው ካካተቷቸው ነጥቦች አንዱም ይህንኑ ሕገ-መንግሥት የተመለከተ ነው።

ለተጨማሪ ከፍተኛ ትምህርት ሎንዶን የሚገኙት አቶ ልደቱ አያሌው ለቪኦኤ ይህንን ቃለ ምልልስ የሰጡት ፓርቲያቸውን ወክለው ሳይሆን በግላቸው መሆኑን አስቀድመን እንገልጻለን።

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከዚህ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውና የሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡ )


XS
SM
MD
LG