በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሊቢያ ተደራዳሪዎች ምርጫ ለማካሄድ ተስማሙ


የሊቢያ ተደራዳሪዎች በሃገሪቱ ለአስር ዓመታት የዘለቀውን ብጥብጥ ለማቆም በተያዘው ንግግር በአንድ ዓመት ከመንፈቅ ጊዜ ውስጥ ምክር ቤታዊና ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ለማካሄድ በወጣው ዕቅድ ላይ ተስማሙ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሊቢያ ተጠባባቂ ልዩ ተወካይ ስቴፈኒ ዊሊያምስ ስምምነቱን ትልቅ ስኬት ብለውታል። በዚህ ሳምንት ቱኒዚያ ላይ በተካሄደው ንግግር የተመድ ሰባ አምስት የሊቢያ ተወካዮች አሰባሰቧል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ምርጫዎች የሚያደራጅ ጊዜያዊ መንግሥት የሚመሰርት ዕቅድ ለማዘጋጀትም እየተሰናዱ መሆናቸው ተገልጿል።

በሌላ የሊቢያ ዜና ለሴቶች መብት ተሟጋች እና ጠበቃ ሊቢያዊት ምስራቅ ሊቢያ ቤንጋዚ ከተማ ውስጥ መኪናቸው ውስጥ እንዳሉ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ።

የአርባ ስድስት ዓመቷ ሃናን አልባራሲ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በመቃወም በማኅበራዊ መገናኛ እና በዜና ማሰራጫ በመሟገት የታጠቁ እና የሴቶች መብት ድርጅት መስርተው የሚታገሉ የነበር ሲሆን በሊቢያ የተመድ ሚሽን ግድያውን አውግዟል።

የሂዩማን ራይትስ ዋች በበኩሉ የምስራቅ ሊቢያ ባለሥልጣናት ይህን በፖለቲካ ምክንያት የተነሳሳ ግድያ በአስቸኳይ እንዲመረምሩ ሲል ጠይቋል።

XS
SM
MD
LG