በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሊቢያውያን ጋዳፊን ከሥልጣን ለመገልበጥ ያቀጣጠሉትን አብዮት ሰባተኛ ዓመት ያከብራሉ


ፎቶ ፋይል፡-ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ
ፎቶ ፋይል፡-ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ

የሊቢያ ሕዝብ፣ አምባገን መሪው የነበሩትን ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊን ከሥልጣን ለመገልበጥ አቅዶ፣ እአአ በየካቲትን 2011 ያቀጣጠለውን አብዮት ሰባተኛ ዓመት ነገ ሐሙስ እንደሚያስብ ተገለጠ።

የሊቢያ ሕዝብ፣ አምባገን መሪው የነበሩትን ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊን ከሥልጣን ለመገልበጥ አቅዶ፣ እአአ በየካቲትን 2011 ያቀጣጠለውን አብዮት ሰባተኛ ዓመት ነገ ሐሙስ እንደሚያስብ ተገለጠ።

ይሁን እንጂ፣ ሀገሪቱ ውስጥ ዛሬም የተለያዩ ግጭቶችና አመፆች እየተካሄዱ ባሉበት ሁኔታ፣ ሊቢያውያን እስካሁንም አብዮታቸው ግቡን እንዳልመታውና ያለመውንም እንዳላሳካ ይናገራሉ።

“የዘንድሮው ዓመታዊ መታሰቢያ ግን፣ ለአንዳንዶቹ ሊቢያውያን የበለጠ መራራና አሳዛኝ” እንደሆነ ተመራማሪዎች ይናገራሉ።

በፍጥነት ወደተቀሩት የሊቢያ ግዛቶች የተዛመተውን የቤንጋዚውን አመፅ ከተከታተሉ ተመራማሪዎች አንዷ፤ሜሪ ፊተጀራልድ ናቸው።

“ከፀረ-ጋዳፊ አብዮት ጋር በተያያዘ በርካታ እንቅስቃሴዎች ተካሂደዋል” የሚሉት እኒሁ ተንታኝ፣ “በተለይ ወጣቱ ትግሉን እስከ አውሮፓ አድርሶታል” ሲሉ ይገልፆታል።

በዚያም ሆነ በዚህ ግን የሊቢያ አብዮት ዛሬ የሕዝቡን ጥያቄ እንዳልመለሰ ነው በብዙ ዜጎች የሚታመነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG