በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊብያ አዲስ የአንድነት መንግሥት ምሥረታ


ሊብያ ውስጥ የሚገኙ ሁለት ተቀናቃኝ ምክር ቤቶች አዲስ የአንድነት መንግሥት ለመመስረት ተስማሙ። ምክር ቤቶቹ ከዚህ ስምምነት የደረሱት፣ በሞሮኮዋ የመዝናኛ ከተማ ስኪራት (Skhirat) ላይ ባካሄዱትና በርካታ መሰናክሎችን በድል በተወጡበት ውይይት ሲሆን፣ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር የሰየሙም መሆናቸው ታውቋል።

ሕዝቡ “ሊብያ! ሊብያ!” እያለ ደስታውን ገልጿል። ይህ የሆነውም የሁለቱ ተቀናቃኝ ምክር ቤቶች አፈ-ጉባዔያት የስምምነቱን ሰነድ በሚፈርሙበትና ከዚያም ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ነው።

ይህ በሁለቱ መካከል የተፈረመው ስምምነት፣ ሊብያን እአአ ከ2011 ወዲህ እሁለት የለያትን ክፍፍል ያስቀረ በመሆኑ ሕዝኑ በታላቅ ደስታ ነው የተቀበለው። እናም ስምምነቱ፣ ሊብያ በ40 ቀናት ውስጥ አዲስ የአንድነት መንግሥት ትመሰርታለች ማለት መሆኑም ተገልጧል።

የሞሮኮው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳላዲን መዙር (Sala’eddin Mezour) በፍርማው ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ነበርና፣ “ስምምነቱ በመፈቃቀድና በስምምነት የመጣ ነው” ብለዋል።

በተጨማሪም “ሊቢያ ልታተኩርበት የሚገባ የዉስጥና የዉጭ የጥቃት ኢላማዎች አሉባት። ምንም እንኩዋን የሚፈለፈዉን ያህል የተሟላ ባይሆንም የህብረት ስምምነቱ የተለያዩ ፓርቲዎች ሊቢያን ተቋማት እንዲገነቡ ጸጥታና መረጋጋትዋን እንዲያረጋግጡ ያደርጋል ነዉ ያሉት” ብለዋል።

ማርቲን ኮብለር (Martin Kobler) በሊብያ የተመድ ልዩ ልዑክ ናቸው። ወደፊት ብርቱ ሥራ የሚጠብቃቸው መሆናቸውን በመግለጽ የአዲሱን የአንድነት መንግሥት መሪ ፈዋዝ ሳራጅን (Fawz Saraj) አስተዋውቀዋል።

በእርስዎን መሆን አልመኝም ልልዎት እወዳለሁ። ከፍተኛ የስራ ብዛት መንግስት ፊት ተደቅኖአል። መጀመሪያ በአገሪቱ ብሔራዊ እርቅ መስፈን ይኖርበታል። ከዚያ የጸጥታዉ ጉዳይ ነዉ። የአሸባሪነትና የዳኢሽ ተዋጊዎች የደቀኑት ችግር አለ። እንዚህ ሁሉ በአስቸኩዋይ መፈታት ያለባቸዉ ችግሮች ናቸዉ።

የተመድ ከአዲሱ የሊብያው አንድነት መንግሥት ጎን እንደሚቆም ያረጋገጡት ኮብለር፣ “ይህ መንግሥት ደግሞ አሉ አክለውም፣ አገሪቱ ውስጥ ይልቁንም ቤንጋዚና በተለያዩ ስፍራዎች ባሉ ስደተኞች ላይ የሚፈጸመውን የከፋ የሰባዊ መብት እረገጣ ለማቆም ብርቱ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል” ብለዋል።

የአዲሱ አንድነት መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ሳራጅ (Saraj) በበኩላቸው፣ ሊብያን ወደ አንድነት ለማምጣት ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ የተጫወተውን ሚና አመስግነዋል።

በስምምነቱ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ፣ የሞሮኮው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳላዲን መዙር (Sala’eddin Mezour) እንዲሁም የተመድ የልብያው ልዩ ልዑክ ማርቲን ኮብለር (Martin Kobler) ተገኝተዋል።

አዲሱ አበበ ያጠናቀረውን ዘገባ ለማዳመት ከዚህ በታች ያለውን የድምች ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

በሊብያ አዲስ የአንድነት መንግሥት ምሥረታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:10 0:00

XS
SM
MD
LG