በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሊቢያ 165 ናይጄሪያውያን ፍልሰተኞችን ወደ አገራቸው መለሰች


ሊቢያ 165 ናይጄሪያውያን ፍልሰተኞችን ወደ አገራቸው መለሰች
ሊቢያ 165 ናይጄሪያውያን ፍልሰተኞችን ወደ አገራቸው መለሰች

ሊቢያ፣ ትላንት ማክሰኞ፣ 165 ናይጄሪያውያንን ወደ አገራቸው መልሳለች፡፡ ይኸው ርምጃ፣ አገሪቱ ሰሞኑን የጀመረችውና ሕገ ወጥ ፍልሰተኞችን ወደ አገራቸው የመመለስ ዘመቻ አካል ነው፤ ተብሏል።

የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት(IOM)፣ ፍልሰተኞቹን የመመለስ ሒደቱን እንደሚቆጣጠር፣ የአሶሺዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል። 165ቱም ፍልሰተኞች፣ ሴቶች እንደኾኑም ታውቋል። የፍልሰት ድርጅቱ፣ አንዳንዶቹ ሴቶች፥ በመንገድ ላይ ልመና ተሠማርተው ነበር፤ ብሏል።

ባለሥልጣናቱ፣ ሌሎችንም የናይጄሪያ ፍልሰተኞች፣ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አገራቸው እንደሚመልሱ ተናግረዋል።

አፍሪካውያን ፍልሰተኞች፣ የሜዲትሬንያን ባሕርን አቋርጦ ወደ አውሮፓ ለመዝለቅ፣ ሊቢያን እንደ መነሻ ይጠቀማሉ።

XS
SM
MD
LG