በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ በሊቢያ እሥር ቤት የሚገኙ እስረኞችን ከሥፍራው አስወጣ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትሪፖሊ ውስጥ በመንግሥት እሥር ቤት የነበሩ ሊብያውያን ስደተኞችን ከቦታው አስወጥቷል። አንዳንዶቹ በእስር ቤቱ ሥላለው መጥፎ ሁኔታ ተቃውሞ በማሰማታቸው ጥቃት ደርሶብናል ካሉ በኋላ ነው የመንግሥታቱ ድርጅት እርምጃውን የወሰደው።

በሊብያ ተቀናቃኝ መንግሥታት መካከል የሚካሄደው ውጊያ በመዲናይቱና በአካባቢው ለሚኖሩ ሲቪሎች እጅግ አደገኛ እንዲሆን አድርጓል።

ትሪፖሊ ያሉትን ስደተኞችና ፍልሰተኞች ከዚህ የከፋ ኑሮ ገጥሟቸው አያውቅም ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተልዕኮ ምክትል ኃላፊ ማቲው ብሩክ ትላንት ተናግረዋል። አደጋ ላይ ያሉት ስደተኞችን ከአካባቢው የማራቁ ተግባር ወሳኝ ነው ብለዋል።

ድርጅቱ ስደተኞቹን ኳሰር ቤን ጋሽር ከተባለው እስር ቤት ለማዛወር የወሰነው አንዳንዶቹ ስደተኞች በተፋፈገ ሁኔታ እንደሚኖሩና ምግብ እንደማያገኙ በመግለፁ ተቃውሞ በማሰማታቸው እንደተደበደቡና በተኩስ እንዳስፈራርዋቸው ከታወቀ በኋላ መሆኑን ገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG