በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሊቢያ ጠ/ሚ ከተቃናቃኛቸው ጋር "አልደራደርም" አሉ


የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፋዬዝ አል ሴራጅ
የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፋዬዝ አል ሴራጅ

ዓለምቀፍ ዕውቅና ያላቸው የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፋዬዝ አል ሴራጅ ከተቃናቃኛቸው ጋር ለመደራደር ፈቃደኛ እንዳልሆኑ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል “እኚህ ሰው በፖለቲካ ሂደቱ አጋር ሊሆኑ እንደማይችሉ ባለፉት ዓመታት የሰሩት ሥራ ይመሰክራል። ስለዚህ እንደገና ቁጭ ቢዬ አላነጋግራችውም“ ብለዋል ።

የጠቅላይ ሚኒስትር አል ሴራጅ እና የተቀናቃኛቸው የጄኔራል ኻሊፋ ሃፍታር ታማኝ የጦር ሰራዊቶች ዋና ከተማዋ ትሪፖሊን ለመቆጣጠር በሚያካሂዱት ውጊያ ብዙ ሺህ ህዝብ ቀዬውን ጥሎ ተሰዷል። ገሚሱም ከተማዋ ውስጥ ባሉ ካምፖች ተጠልሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አል ሰራጅ ባለፈው የካቲት ጄኔራል ሃፍታር ማነጋገሬ በአውሮፕላን ትሪፖሊን በቦምብ ለማስደብደብ እንዲዘጋጁ ጊዜ ከመስጠት ሌላ የፈየደው ነገር የለም ማለታቸው ተጠቅሷል።

አሁን ዋናው ግባችን ትሪፖሊን ከጥቃት መከላከል ነው ያሉት አል ሲራጅ በጥቂት ቀናት ውስጥ ውጤቱን ታያላችሁ ብለዋል። ዝርዝር ውስጥ አልገቡም። ጄኔራል ሃፍታር ምላሽ አልሰጡም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG