በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሊቢያ 200 የሚሆኑ ፍልሰተኞችን ከአገሯ አባረረች


የሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ
የሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ

ሊቢያ ከግብፅ፣ ቻድ እና ሱዳን የመጡ 200 የሚሆኑ ፍልሰተኞችን ሰብስባ አገራቸው ድንበር ላይ ጥላለች።

የፍልሰተኞቹን አገር ለመለየት የተለያየ ቱታ አንዳለበሷቸውና ከዛም በአውቶብስ አገራቸው ድንበር ላይ እንደጣሏቸው የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

የየአገራቱ አምባሳደሮች የሽኝት ሂደቱን ቆመው መታዘባቸውንም ዘገባው ጠቁሟል።

105 ግብጻውያን፣ 101 የቻድ ዜጎች እንዲሁም 20 ሱዳናውያን መሆናቸውም ታውቋል።

ፍልሰተኞቹን የማስወጣቱ ሥራ በሊቢያ መንግሥትና በተቃዋሚዎች መካከል ያልተለመደ ሥምምነት የተደረገበት ነው ተብሏል።

በጦርነት ወደ ወደመችው ሊቢያ በሺህ የሚቆጠሩ አፍሪካውያን የሣሃራ ባህርን አቋርጠው ይገባሉ።

ተስፋ የሚያደርጉት ሜዲትሬንያን ባህርን አቋጠተው ወደ አውሮፓ መግባት ነው።

XS
SM
MD
LG