በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊቢያ 28 ፍልሰተኞች በጅምላ ተቀብረው ተገኙ


በሊቢያ ደቡብ ምሥራቅ ኩፍራ በተባለ አውራጃ የ28 ፍለሰተኞች አስከሬን በአንድ ሥፍራ ተቀብሮ መገኘቱን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
በሊቢያ ደቡብ ምሥራቅ ኩፍራ በተባለ አውራጃ የ28 ፍለሰተኞች አስከሬን በአንድ ሥፍራ ተቀብሮ መገኘቱን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

በሊቢያ ደቡብ ምሥራቅ ኩፍራ በተባለ አውራጃ የ28 ፍለሰተኞች አስከሬን በአንድ ሥፍራ ተቀብሮ መገኘቱን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ሥፍራው ፍልሰተኞቹ ታግተው ሰቆቃ ሲፈጸምባቸው የነበረ መሆኑም ተመልክቷል። ፍልሰተኞቹ ከሰሃራ በታች ካሉ ሃገራት የሄዱ እንደኾነም ታውቋል።

የሃገሪቱ የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ እንዳስታወቀው የመቃብር ሥፍራው የተገኘው የሕገ ወጥ ዝውውር ሰለባ የሆኑ ፍልሰተኞች ታግተው ሰቆቃ የሚፈጸምባቸው ሥፍራዎች ላይ ባደረጉት አሰሳ ነው። ከሰሃራ በታች ካሉ ሃገራት የሄዱና ታግተው ሰቆቃ ሲፈጸምባቸው የነበሩ ሰባ ስድስት ፍልሰተኞችን ነጻ ማውጣታቸውንም ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

አንድ ሊቢያዊና ሁለት የሌሎች ሃገራት ዜጎች መያዛቸውም ተመልክቷል።

የሃገሪቱ የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ካወጣው መግለጫ ጋራ የተያያዘው ፎቶግራፍ፣ ነጻ የውጡት ፍልሰተኞች ገርጥተው፣ በፊታቸውና በሌሎችም የሰውነት ክፍሎቻቸው ላይ ጠባሳ እንዳለባቸው አሳይቷል።

በእ.አ.አ 2011 በሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ሀገራት ደጋፊነት በተነሳው አመጽ፣ የረጅም ጊዜ መሪው ሞአመር ጋዳፊ ከሥልጣን ከተወገዱ ወዲህ ሊቢያ ከሁከት አልተለየችም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG