በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊቢያ በጅምላ መቃብር 18 አስከሬኖች ተገኙ


ሲርት
ሲርት

በሊቢያ ባንድ ወቅት የእስላማዊ መንግሥት ቡድን ጠንካራ ይዞታ በነበረችው ማዕከላዊ የጠረፍ ከተማ ሲርት በጅምላ መቃብር የተቀበሩ አስራ ስምንት አስከሬኖች መገኘታቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ደብዛቸው የጠፋ ሰዎች ጉዳይ ባለሥልጣን የተባለው የመንግሥቱ መሥሪያ ቤት ዕሁድ ዕለት ባወጣው መግለጫ የጅምላ መቃብሩ ተቆፍሮ አጽሞቹን ማንነታቸውን በምርመራ ለማወቅ በከተማዋ ወደሚገኝ ሆስፒታል ተወስደዋል ብሏል።

የቀድሞው የሊቢያ አምባገነን መሪ የሙአመር ጋዳፊ የትውልድ ከተማ የሆነችውን ሲርትን የእስላማዊ መንግሥት ቡድን ታጣቂዎች እአአ ከ2015 እስከ 2016 ተቆጣጥረዋት እንደነበር ይታወሳል።

በቅርብ ጊዜያት ሊቢያ ውስጥ በርካታ የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸው ተመልክቷል።

XS
SM
MD
LG