በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሊቢያ ሰላም በፓሪስ ጉባዔ እየተካሄደ ነው


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዛሬ ፓሪስ ላይ የተሰባሰቡት የሊቢያ ተቀናቃኝ መሪዎች እና ከሃያ በላይ ሃገሮች ዲፕሎማቶች በጦርነት የዳሸቀችው ሃገር በዘንድሮ የአውሮፓውያን ዓመት መጨረሻ ምርጫ መካሄድ እንዳለባት በመርህ ተስማምተዋል።

ዛሬ ፓሪስ ላይ የተሰባሰቡት የሊቢያ ተቀናቃኝ መሪዎች እና ከሃያ በላይ ሃገሮች ዲፕሎማቶች በጦርነት የዳሸቀችው ሃገር በዘንድሮ የአውሮፓውያን ዓመት መጨረሻ ምርጫ መካሄድ እንዳለባት በመርህ ተስማምተዋል።

የፓሪሱ ጉባዔ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሊቢያ ሰላም እንዲሰፍን ለሁለተኛ ጊዜ ያደረጉት ጥረት መሆኑ ነው።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚደገፈው የትሪፖሊው መንግሥት መሪ ፋዬዝ አል ሳራጅ፣ የጦር ሰራዊታቸው ምሥራቅ ሊቢያ የሚቆጣጠረው የሰባ አምስት ዓመቱ ሓሊፋ ሃፍታር እና መቀመጫውን ምሥራቅ ሊቢያ ያደረገው ፓርላማ አፈ ጉባዔ በሀገሪቱ እኤአ ታህሳስ 10 ቀን ፕሬዚዳንታዊ እና ምክርቤታዊ ምርጫ መካሄድ እንዳለበት ማወጃቸውን የፈረንሳይ ባለሥልጣናት ገልጠዋል።

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ማክሮን ጉባዔው ከመጀመሩ አስቀድሞ ባደረጉት ንግግር ለራሳችን ጥቅም እና ደኅንነት ስንል ሊቢያ እንድትረጋጋ መሥራት አለብን ማለታቸው ተጠቅሷል።

አንዳንድ ተንታኞች በበኩላቸው የፈረንሳዩን ፕሬዚዳንት ትዕግስት አጥተው እንጂ እንጂ በጦርነት የዳሸቀችው ሃገር ሁኔታ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድ አመቺ አይደለም በማለት ሲነቅፉ ተሰምተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG