የሊቢያ ባለሥልጣናት ያለሕጋዊ ፈቃድ የገቡ 350 ግብጻውያን ፍልሰተኞችን ወደሀገራቸው መመለስ መጀመራቸውን አስታወቁ፡፡
ጦርነት ያዳሸቃት ሊቢያ ወደ አውሮፓ ለመግባት አደገኛ ጉዞ የሚያደርጉ አፍሪካውያን ፍልሰተኞች ዋና መነሻ ሆናለች፡፡ የሊቢያ ተቀናቃኝ መንግሥታት ትሪፖሊ የሚገኘው ጸረ ፍልሰተኛ ተቋም በህገ ወጥ መንገድ የገቡ የውጭ ሀገር ሰዎችን እንዲያስወጣ ባለፈው ዓመት ስምምነት ላይ መድረሳቸው አይዘነጋም፡፡
ባለፈው ማክሰኞ የሚበዙት ሴቶች የሆኑ 323 ፍልሰተኞች ከትሪፖሊ እና ከቤንጋዚ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ጋር በመተባበር ወደናይጄሪያ ተመልሰው የተላኩ ሲሆን የሊቢያው ጸረ ፍልሰተኛ ተቋም ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል ሃይታም ቤልጋሴም አማር በሰጡት በቀጣዮቹ ቀናትም ፍልሰተኞችን ማስወጣት እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ሊቢያ ባለፈው ህዳር 600 በታህሣስ ደግሞ 650 ግብጻውያን ፍልሰተኞችን ወደሀገራቸው መልሳለች፡፡
ብዙዎቹ ግብጻውያን ወደሊቢያ የሚሄዱት በባሕር ወደአውሮፓ ለመጓዝ አልመው ቢሆንም ለብዙ ዓመታት እዚያው ሊቢያ ቀርተው በግብርና እና በግንባታ ሥራ ተቀጥረው የሚኖሩ ብዙ ሺህ ግብጻውያን ፍልሰተኞችም አሉ፡፡
መድረክ / ፎረም