የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውሳኔን መሰረት በማድረግ United States ፈረንሳይና ብሪታንያ
የሚገኙባቸው የተባበሩት ሃይሎች በሊብያ ላይ በረራ የሚታገድበት ቀጠና በመመስረት ሊብያውያን
ሲቪሎችን ከሀገሪቱ መሪ ሞዐማር ጋዳፊ ወታደሮች ጥቃትና ግድያ ለመከላከል በሚል በሊብያ ወታደራዊ
እርምጃ መውሰድ ከጀመሩ ከሳምንት በላይ ሆኗል።
በካናዳ ኮንኮርዲያ ዩኒቨርሲቲ የመካከላኛው ምስራቅ ጉዳይ ፕሮፌሰር ጳውሎስ ሚልኪያስ ለለጉዳዩ
እንዲያብራሩልን የአፍሪቃ ነክ ርዕስች አዘጋጅና አቅራቢ አዳነች ፍሰሀየ ጋብዛለች። ፕሮፌሰር ጳውሎስ
የህብረት ሀይሎቹ ወታደራዊ እርምጃ ሰፋትና ክብደት የረጂም ማለት የመንግስት ለውጥን የሚያካትት
ይመስላል ስለሚለው ነጥብ በማብራራት ይጀምራሉ።