በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊብያ እስር ቤት ላይ በተፈፀመ የአየር ጥቃት ፍልሰተኞች ተገደሉ


ከሊብያ መዲና ወጣ ብሎ በሚገኘው ፍልሰተኞች የታሰሩበት ቦታ ላይ የተፈፀሙት የአየር ድብደባዎች ቢያንስ የ40 ሰዎችን ህይወት በማጥፋታቸው በጦርነት ወንጀል ደረጃ ሊታይ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሊብያ ልዑክ አስገንዝቧል።

የአየር ድብደባዎቹ በሁኔታዎች ተገደው የተጠለሉትን ንፁሃን ሰዎችን የገደሉ በመሆናቸው የጦርነት ወንጀል ሊሆኑ እንደሚችሉ ግልፅ ነው” ሲሉ ገሃሰሳን ሰላሚ ዛሬ ባወጡት መግለጫ ገልፀዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽነርና የአፍሪካ ህብረት ከ130 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ያቆሰሉትን የአየር ድብደባዎችን አውግዘዋል።

የሊብያ የጤና ጥበቃ ባለሥልጣኖች ትላንት ማታ በተካሄዱት የአየር ድብዳባዎች ከተገደሉት ሰዎች ሌላ 80 ሰዎች መቁሰላቸውን ተናግረዋል።

ጥቃቶቹ ከተፈፀሙ በኋላ ሲቪሎች ዒላማ መሆን የለባቸዋም፣ ፍልሰተኞችና ስደተኞች መታሰር አይገባቸውም፣ በሜዲትራንያን ባህር በኩል አውሮፓ ለመግባት ሞክረው ከአደጋ እንዲተርፉ የተደረጉትን ፍልሰተኞች ወደ ሊብያ እንደሚለሱ መገደድ የለባቸውም። ምክንያቱም ሊብያ ለደኅንነታቸው አስተማማኝ ሀገር አይደልችምና ሲሉ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ አስገንዝበውል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG