በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የላይቤሪያ ፕሬዚዳንታዊ ማጣሪያ ምርጫ ላልተወሰነ ጊዜ ተላለፈ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የላይቤሪያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ ሳምንት ውስጥ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረውን ፕሬዚዳንታዊ ማጣሪያ ምርጫ ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፎታል። በመጀመሪያው ዙር ምርጫ የማጭበርበር ተግባር ተፈፅሙዋል የሚል ስጋት በመኖሩ መሆኑን አመልክቷል፡፡

የላይቤሪያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ ሳምንት ውስጥ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረውን ፕሬዚዳንታዊ ማጣሪያ ምርጫ ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፎታል። በመጀመሪያው ዙር ምርጫ የማጭበርበር ተግባር ተፈፅሙዋል የሚል ስጋት በመኖሩ መሆኑን አመልክቷል፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የመሃል ዳኛ ፍራንሲስ ሴይ ኮርክፖር ዛሬ ባሰጡት ብይን ባለፈው ጥቃምት ወር በተካሄደው የመጀመሪያው ዙር ድምፅ አሰጣጥ የተመለከቱ አቤቱታዎች እያሉ የምርጫው ኮሚሽን ማጣሪያ ምርጫ ለማካሄድ መወሰኑ ስህተት እና ህገወጥ ዕርምጃ ነው ብለዋል።

ሁለቱ ዋና ዋናዎቹ ዕጩ ተፎካካሪዎች የቀድሞ የእግር ኳስ ኮከብ ጆርጅ ዊያ እና ምክትል ፕሬዚደንት ጆሴፍ ቦካይ በማጣሪያው ምርጫ ሊካፈሉ ተዘጋጅተው የነበረ ሲሆን ባለፈው ምርጫ ሦስተኛ የሆኑት ቻርልስ ብሩምስኪን መጠነ ሰፊ የማጨበር ተግባር ተፈፅሟል ብለው በፍርድ ቤት ክስ ከፍተዋል።

ሁለተኛው ዙር መቼ እንደሚከናወን ቀን አልተቆረጠም የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛም ያሉት አቤቱታዎች መልስ ሳያገኙ የማጣሪያው ቀን አይወሰንም ብለዋል፡፡

የምርጫው ተፎካካሪዎች የሚወዳደሩት ፕሬዚደንት ኤሌን ጆንሰንን ለመተካት ነው። ለሁለት የሥልጣን ዘመን ያገለገሉት ጆንሰን በሚቀጥለው ጥር ወር ይሰናበታሉ፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG