ዋሺንግተን ዲሲ —
በላይቤሪያው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት መሠረት፣ ምክትል ፕሬዚደንቱ ጆሴፍ ቦካይ እና ታዋቂው የእግር ኳስ ተጫዋች ጆርጅ ዊሃ በቀዳሚነት ይገኛሉ፤ የምርጫ ባለሥልጣናት እንደገለፁት ግን፣ ካለፈው ማክሰኞ አንስቶ እስከ ትናንት ሐሙስ ባሉት የሦስት ቀናት የተቆጠረው ድምፁ አንድ ሦስተኛው ብቻ ነው።
የሌበሪቲ ፓርቲ ግን፣
“የድምጽ አቆጣጠሩ የተጭበረበረ በመሆኑ” ቆጠራው እንዲቆም መጠየቁ ተሰምቷል።
ላይቤሪያውያን፣ ሁለት ጊዜ የተመረጡት የኖቤል ሰላም ተሸላሚና የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሴት መሪ ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ ከ6 ዓመታት በኋላ ሥልጣን ሲለቁ ሊተካቸው የሚችል ፕሬዚደንት በአገሪቱ ህገ መንግሥት መሠረት ለመምረጥ ድምፃቸውን እየሰጡ ናቸው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ