በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጆርጅ ዊያ እንደገና ለመመረጥ የሚሞክርበት ምርጫ በላይቤሪያ ተካሄደ


ሊቤሪያውያን ድምጽ እየሰጡ እአአ ጥቅምት 10/2023
ሊቤሪያውያን ድምጽ እየሰጡ እአአ ጥቅምት 10/2023

ላይቤሪያውያን ትናንት ድምጽ ሰጥተዋል። ታዋቂው የቀድሞ የእግር ኳስ ተጫዋች እና የወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ጆርጅ ዊያ እንደገና ለመመረጥ ጥረት በማድረግ ላይ ነው።

በተደጋጋሚ የእርስ በእርስ ጦርነት ጉዳት በደረሰባት የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር፣ ሠላም የመራጮች ዋና ትኩረት ነው ተብሏል።

ዋናዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው በሠላም እንደሚያልፍ ቃል ገብተዋል። ባለፈው ወር በደጋፊዎቻቸው መካከል በተፈጠረ ግጭት 3 ሰዎች መሞታቸው ግን፣ ሁከት ተመልሶ እንዳይመታ ስጋት ፈጥሯል።

የባሎን ዶር ብቸኛው አፍሪካዊ ተሸላሚ የሆነው የ 57 ዓመቱ ጆርጅ ዊያ፣ ከስድስት ዓመታት በፊት በፕሬዝደንትነት ሲመረጥ፣ ሥራን እንደሚፈጥር እና በትምሕርት ላይ መዋዕለ ነዋይ እንደሚያፈስ ቃል ገብቶ ነበር። ነቃፊዎቹ ቃሉን አልጠበቀም ሲሉ ይከሳሉ።

በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የቀረበውን የጦር ወንጀል ፍ/ቤት እንዲቋቋም የቀረበውን ጥያቄም ተገባራዊ አላደረገም።

የአውሮፓ ኅብረት፣ የአፍሪካ ኅብረት፣ ኤኮዋስ እና አሜሪካ የምርጫ ታዛቢዎቻቸውን እንደላኩ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG