በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ድምፅ "የአፍሪካ ሙዚቃ ሰዓት አባት" ሊዬ ሳርኪስያን

የአሜሪካ ድምፅ "የአፍሪካ ሙዚቃ ሰዓት አባት" ሊዬ ሳርኪስያን በተወለደ በ97 ዓመት ዕድሜው አረፈ። “ለሙዚቃ ይልቁንም ለአፍሪካ ሙዚቃ ያለው ፍቅር ወደር አልነበረውም” የቪኦኤ የአፍሪካ ዋና ክፍል ዳይሬክተር ንጉሴ መንገሻ እአአ በ1960 መጀመሪያ በጊኒ “ቀዳሚ የአፍሪካ የሙዚቃ ሰው” በሚለው መጠሪያው የተወቀው ሊዬ፣ እአአ በ1963ዓም ነው፤ ለአሜሪካ ድምፅ መሥራት የጀመረው።

የአሜሪካ ድምፅ "የአፍሪካ ሙዚቃ ሰዓት አባት" ሊዬ ሳርኪስያን በተወለደ በ97 ዓመት ዕድሜው አረፈ።
“ለሙዚቃ ይልቁንም ለአፍሪካ ሙዚቃ ያለው ፍቅር ወደር አልነበረውም” የቪኦኤ የአፍሪካ ዋና ክፍል ዳይሬክተር ንጉሴ መንገሻ
እአአ በ1960 መጀመሪያ በጊኒ “ቀዳሚ የአፍሪካ የሙዚቃ ሰው” በሚለው መጠሪያው የተወቀው ሊዬ፣ እአአ በ1963ዓም ነው፤ ለአሜሪካ ድምፅ መሥራት የጀመረው።
ለአህጉሪቷና ለባህሏ፣ እንዲሁም ለሕዝቧ ልዩ ፍቅር የነበረው ሊዬ ከአሥራ ሦስት ዓመታት አገልግሎት በኋላ እአአ በ1976 ጡረታ ከተገለለ በኋላ ዳግም ከአሜሪካ ድምፅ ጋር መደበኛ ያልሆነ ቅጥር በመፈፀም፤ በ91 ዓመቱ ሙሉ በሙሉ ሥራውን እስካቆመበት እአአ በ2012 ድረስ ለተጨማሪ 36 ዓመታት አግልግሏል።
ሊዬ በርካታ የጅማት ክሮች ያሉትን ካኑን በመባል የሚታወቀውን የክር ሙዚቃ መሳሪያና ጊታር ግሩም አድርጎ ይጫወታል። የቅብ እና የእርሳስ የሥዕል ሥራዎቹም በተለያዩ የአፍሪካ እና በአውሮፓ ከተሞች ለትዕይንት በቅተውለታል።
የሙዚቃው ሰው ሊዬ ባደረበት ሕመም በተወለደ በዘጠና ሰባት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG