በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያና የሱዳን መሪዎች ናይሮቢ ተወያዩ


የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶና የሱዳኑ የሽግግር ምክር ቤት መሪ ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ናይሮቢ፣ ኬንያ
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶና የሱዳኑ የሽግግር ምክር ቤት መሪ ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ናይሮቢ፣ ኬንያ

የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶና የሱዳኑ የሽግግር ምክር ቤት መሪ ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ናይሮቢ ላይ ተገናኝተው በሱዳንና በቀጣናው የፀጥታ ሁኔታ ላይ ተነጋግረዋል።

ሱዳን ላለችበት ሁከት መፍትኄ እንዲፈለግና በአጠቃላይም ግጭቶችን ማስቆም በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ለመምከር የምሥራቅ አፍሪካ የጋራ ልማት ባለስልጣን (ኢጋድ) በአስቸኳይ ሰፊ የሰላም ሂደት ሁኔታዎችን እንዲያመቻች አሳስበዋል።

በሱዳን ጦርና ብርቱ ነው በሚባለው ውትድርና ቀመስ ቡድን መካከል ለሰባት ወራት ያህል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ከፍተኛ ውድመት ማስከተሉ ተዘግቧል።

ከግማሽ በላይ የሚሆነው የሱዳን ሕዝብ ለእርዳታ ጠባቂነት የተዳረገ ሲሆን ዳርፉር ውስጥም ከሃያ ዓመት በፊት ተካሂዶ ብዙ ዕልቂት እንዳደረሰው ዓይነት ግጭት ዳርፉር ውስጥ እንዳያገረሽ ሥጋት ተፈጥሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG