በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወድቀው የራስ ጉዳት የደረሰባቸው መካኔል ሆስፒታል ይቆያሉ


የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የአናሳዎቹ ሪፐብሊካን እንደራሴዎች መሪ ሚች መካኔል
የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የአናሳዎቹ ሪፐብሊካን እንደራሴዎች መሪ ሚች መካኔል

የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የአናሳዎቹ ሪፐብሊካን እንደራሴዎች መሪ ሚች መካኔል ዋሺንግተን፤ ዲ.ሲ ውስጥ በሚገኘውና ቀድሞ ትረምፕ ኢንተርናሽናል ይባል በነበረው የአሁኑ ዋልዶርፍ አስቶሪያ ሆቴል ውስጥ ወድቀው በደረሰባቸው ጉዳት የጤና ክትትልና እንክብካቤ ለማግኘት ለጥቂት ቀናት በሆስፒታል እንደሚቆዩ ቃል አቀባያቸው ዛሬ፤ ሃሙስ አስታውቀዋል።

የ81 ዓመቱ የኬንታኪው ሴኔተር ተደናቅፈው በወደቁበት ትናንት ረቡዕ ምሽት እርሳቸውን የሚደርግፈው የምክር ቤቱ አመራር የገንዘብ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ የራት ሥነ ሥርዓት ላይ እንደነበሩ ተገልጿል።

መኮኔል ፈጥነው እንዲያገግሙ የተመኙላቸው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ወደ ምክር ቤት ተመልሰው ሊያይዋቸው እንደሚጓጉ ባስተላለፉት የትዊት መልዕክት አስታውቀዋል።

የህክምና ባለሙያዎች ለመካኔል ለሚያደርጉት እንክብካቤና የሥራ ባልደረቦቻቸው ላሳዩት ልባዊ ምኞት ቃል አቀባያቸው ዴቪድ ፓፕ አድናቆት ገልፀዋል።

መካኔል ስላሉበት የጤንነት ሁኔታም ሆነ ወደ ምክር ቤቱ መቼ እንደሚመለሱ ፅህፈት ቤታቸው ተጨማሪ መረጃ አልሰጠም።

መካኔል ያጋጠማቸው በራስ ላይ የሚደርስ አደጋን ተክትሎ በግጭት ምክንያት የሚደርስ መናጋት መሆኑ በዘገባው የተመለከተ ሲሆን ከጉዳቱ ለማገገም ጊዜ እንደሚወስድ ተገልጿል።

እኤአ በ2019 የሪፐብሊካኑ መሪ መካኔል በኬንተኪ ክፍለ ግዛት ውስጥ ባለው ቤታቸው ውስጥም እንዲሁ አደናቅፏቸው ወድቀው እንደነበረ ተዘግቧል።

ብዙዎቹ የፕሮፌሽናል ስፖርት ማኅበራት ትኩረታቸውን በተደጋጋሚ በራስ ላይ በሚደርሰው የመናጋት ጉዳት ላይ ማድረጋቸውም ተነግሯል።

ኮንግረሱ ለመፀው ወራት የሚዘጋበት ጊዜ ስለሆነ መካኔል ከጉዳታቸው ሲያገግሙ ከቤታቸው እንደሚሠሩ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG