በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ባአርመኒያ-አዘርባጃን ስብሰባ ላይ ለመገኘት ኢራን ገብተዋል


የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፣ የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ጋር በቴህራን ኢራን እአአ እአአ 23/2023
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፣ የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ጋር በቴህራን ኢራን እአአ እአአ 23/2023

የሩሲያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ፣ በአርመኒያ እና አዘርባጃን የሠላም ሂደት ላይ በሚመክረው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ኢራን መዲና ቴህራን ገብተዋል።

የኢራን፣ ቱርክ፣ እና የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከአርመኒያ እና አዘርባጃን አቻዎቻቸው ጋር፣ በሁለቱ ሃገራት መካከል የሰላም ስምምነት እንዲኖር የሚደረገው ጥረት የደረስበትን ደረጃ በተመለከተ ይወያያሉ ተብሏል።

የሩሲያ አርመኒያ እና አዘርባጃን የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች፣ የአዘርባጃን ኃይሎች በናጎርኖ ካራባክ ላይ ባለፈው መስከረም ጥቃት ከሰነዘሩ ወዲህ ሲገናኙ የመጀመሪያው እንደሆነ ተነግሯል።

ሀገራቱ የአካባቢያቸውን ጉዳይ ካለምዕራባውያኑ ጣልቃ ገብነት ለመነጋገር እንደሚሹ፣ የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቋል። አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረትን የሚመለከት መሆኑን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል። አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት ሁለቱን ወገኖች ለማሸማገል መሞከራቸው ሞስኮብን ያበሳጨ ጉዳይ ነበር ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG