በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቱርክና ሦሪያ በድጋሚ የተከሰተው ርዕደ-መሬት የረድኤት ሥራ እያስተጓጎለ ነው


በቱርክና ሦሪያ በድጋሚ የተከሰተው ርዕደ-መሬት
በቱርክና ሦሪያ በድጋሚ የተከሰተው ርዕደ-መሬት

ባለፈው ሰኞ በቱርክና በሰሜን ምዕራብ ሦሪያ በድጋሚ የተከሰተው ርዕደ መሬት የረድኤት ሠራተኞችን ሥጋት ላይ በመጣሉ በመቶ ሺህ ለሚቆጠሩ ሰዎች ምግብ የማከፋፈሉን ሥራ አወሳስቧል ሲል የተመድ የምግብ ፕሮግራም (ፋኦ) አስታወቀ፡፡

የረድኤት ሠራተኞቹ እጅግ ቀዝቃዛ በሆነው በዚህ ወቅት መኪናቸው ውስጥ እያደሩ ምግብ ያማዳረስ ሥራቸውን ለማከናወን እየጣሩ ነው ሲል የምግብ ፕሮግራሙ አስታውቋል፡፡

ፕሮግራሙ ለሠራተኞቹ ማረፊያ አዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም፣ ሰኞ ዕለት የተከሰተውና በሬክተር መለኪያ 6.4 የሆነው ርዕደ መሬት እንደገና ወደ ውጪ እንዲወጡ እንዳደረገ የምግብ ፕሮግራሙ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡

በሰኞው የመሬት መናወጥ ስምንት ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል፡፡ ንዝረቱ በጆርዳን፣ እስራኤል፣ ሌባኖስና ግብጽ ተሰምቷል፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት በቱርክና በሦሪያ በደረሰው መናወጥ 45 ሺህ ሰዎች መሞታቸው ታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG