በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢቦላ በኮንጎ


በኮንጎ ዲሞክርስያዊ ሪፖብሊክ ምዕራባዊ ክፍል፣ በኢቦል ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር፣ ከሁለት ዓመታት በፊት፣ በአካባቢው ከነበረው የበዛ መሆኑን፣ የዓለም የጤና ድርጅት ባለሥልጣኖች ትናንት ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት በምዕራባዊው ክፍል፣ 56 የኢቦላ በሽተኞች እንዳሉ፣ በአፍሪካ የዓለም የጤና ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ማተሺዲሶ ሞየቲ ገልጸው፣ በተለይም በአካባቢው ከዚህ ቀደም ከነበረው የበዛ መሆኑ ያሳስበናል ብለዋል።

ኢኳቱር ስለተባለው የኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክን፣ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፖብሊክ ጋር ስለሚዋሰነው ሰፊ ክፍለ ሃገር ነው የሚናገሩት። ከሁለት ዓመታት በፊት፣ በአካባቢው በኢቦላ የተያዙ ሰዎች ቁጥር፣ 54 እንደነበርና እንቅስቅሴን በማገድ፣ ከዛ እንዳይበዛ ለማድረግ ተችሎ እንደነበር፣ ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል። ዓለምቀፉ ወረሽኝ ኮቪድ-19 በተዛመተበት በአሁኑ ወቅት፣ ኢቦላን የመከላከሉ ጥረት በአቅርቦት እጥረትና በቦታው አቀማመጥ ችግር ምክንያት ከባደ መሆኑን ሞየቲ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG