በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ላስ ቬጋስ በደረሰ ጥቃት የሞትና የመቁሰል አደጋ ተከስቷል

ዩናይትድ ስቴትስ ኔቫዳ ክፍለ ሃገር ላስ ቬጋስ ከተማ ውስጥ አንድ አጥቂ ትናንት ዕሁድ ማታ በካንትሪ ሙዚቃ ዝግጅት ላይ ተኩስ ከፍቶ ቢያንስ ሃምሳ ሰው ገድሎ ከአራት መቶ በላይ ማቁሰሉን ፖሊሶች አስታወቁ።

ዩናይትድ ስቴትስ ኔቫዳ ክፍለ ሃገር ላስ ቬጋስ ከተማ ውስጥ አንድ አጥቂ ትናንት ዕሁድ ማታ በካንትሪ ሙዚቃ ዝግጅት ላይ ተኩስ ከፍቶ ቢያንስ ሃምሳ ሰው ገድሎ ከአራት መቶ በላይ ማቁሰሉን ፖሊሶች አስታወቁ።

ጥቃቱ በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ በጅምላ የተኩስ ጥቃት በተገደሉ ሰዎች ብዛት ከምንጊዜውም ከፍተኛው መሆኑ ታውቁዋል።

የላስቬጋስ ከተማ ፖሊስ እንደገለጠው አጥቂው እዚያችው ኔቫዳ ክፍለ ግዛት መስኩዊት ከተማ የሚኖር ስቴፈን ፓዶክ የሚባል የስድሳ አራት ዓመት ዕድሜ ያለው ነጭ ነው።

ታጣቂው ማንዳሌይ ቤይ በሚባለው ባለቁማር መዝናኛ ሆቴል ሰላሳ ሶስተኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ክፍሉ ላይ ሆኖ ከመንገድ ባሻገር ሙዚቃ ዝግጅት ለማየት ሜዳ ላይ በተሰበሰበ ሃያ ሁለት ሺህ ሰው ላይ ሲተኩስ ሰዉ እየተጩዋጩዋኸ ሲደበቅና ሲሮጥ ቪዲዮ ታይቱዋል።

የላስ ቬጋስ ፖሊስ ጆሴፍ ሎምባርዶ በሰጡት ልዩ ስልጠና ያላቸው ፖሊሶች የአጥቂውን የሆቴል ክፍል ሰብረው ሲገቡ ሞቶ አግኝተውታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG