በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በላስ ቬጋስ ኢትዮጵያውያን የበዙበት አካባቢ “ትንሿ ኢትዮጵያ” በሚል እንዲሰየም ተወሰነ


በላስ ቬጋስ ኢትዮጵያውያን የበዙበት አካባቢ “ትንሿ ኢትዮጵያ” በሚል እንዲሰየም ተወሰነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:40 0:00

በላስ ቬጋስ ኢትዮጵያውያን የበዙበት አካባቢ “ትንሿ ኢትዮጵያ” በሚል እንዲሰየም ተወሰነ

የላስ ቬጋስ ከተማ ክላርክ ወረዳ ኮሚሽን፣ ባለፈው ሳምንት ተሰብስቦ፣ ኢትዮጵያውያን በዝተው የሚኖሩበት አካባቢ፣ “ትንሿ ኢትዮጵያ” የሚል ስያሜ እንዲያገኝ ውሳኔ አሳልፏል።

በኒቫዳ ላስሼጋስ ከተማ፣ “ትንሽዋ ኢትዮጵያ” ተብሎ የሚጠራው የመንገድ ስያሜ፣ በከተማዋ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መጽደቁንና ይህንኑም ሥራ ላይ ለማዋል በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ፣ በላስቬጋስ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ንኡስ ኮሚቴ አባላት አስታወቁ።

የዚኹ ኮሚቴ አስተባባሪ እና ሊቀ መንበር አቶ ግርማ ዘይድ በሰጡት ማብራርያ፣ ኮሚቴው፥ ይህን ስያሜ ለማጸደቅ፣ ብዙ ውጣ ውረዶችን እንዳለፈና እልክ አስጨራሽ እንደነበር ተናግረዋል።

የስያሜው መጽደቅ፣ በከተማዋ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ኾነ ለውጭ አገር ዜጎች ላቅ ያለ ጠቀሜታ እንደሚሰጥና የኢትዮጵያን ባህል በማስተዋወቁ ረገድ ክፍተኛ እስተዋፅኦ እንደሚኖረው፣ በንግድ እና በመሳስሉት ሥራዎች ላይ የተሠማሩት የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በዚኹ የመንገድ ስያሜ በተሰጠው ሥፍራ፣ ዐዲስ ማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጥባቸውን ተቋማት ለማሳደግ ዕቅድ እንዳለም፣ በንኡስ ኮሚቴው ማብራርያ ተጠቁሟል። በላስ ሼጋስ፣ ወደ 40 ሺሕ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ነዋሪዎች እንደሚገኙ ይታውቃል።

የዘገባውን ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG